Fana: At a Speed of Life!

መንግስት የዜጎችን ደህንነት ለማስጠበቅ ቁርጠኝነት ብቻም ሳይሆን አቅም አለው- ጠ/ሚ አብይ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 2፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) መንግስት የዜጎችን ደህንነት ለማስጠበቅ ቁርጠኝነት ብቻ ሳይሆን አቅም እንዳለው የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ አስታወቁ፡፡

አዲስ ወግ ሁለት የህግ የበላይነት በዴሞክራሲ ሽግግር ሂደት በሚል ርዕስ በዛሬው ዕለት በጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት አዘጋጅነት ተካሂዷል፡፡

በዚህ ወቅት የተገኙት ጠቅላይ ሚኒስትሩ መንግስት ሕጋዊ የሕግ አስከባሪ ነው ለዚህም የሚያስከብርበት የሕግ አውድና የሚያስፈፅምባቸው ጠንካራ ተቋማት መኖራቸው የአመራሩን የሕግ የበላይነትን ማክበር ወይም በሕግ የመገዛት አዝማሚያ አመላካቾች ናቸው ብለዋል።

መንግስት የዜጎች ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅ ፈጣን ምላሽ እየሰጠ አይደለም በማለት ከተሳታፊዎች ለተነሳው ጥያቄም ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

ከማንም በላይ መንግስት ትዕግስተኛ መሆን አለበት ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ መንግስት የዜጎችን ደህንነት ለማስጠበቅ ቁርጠኝነት ብቻ ሳይሆን አቅምም እንዳለው አስረድተዋል።

You might also like
Comments
Loading...