Fana: At a Speed of Life!

ሁዋዌ በመጀመሪያው ሩብ ዓመት 59 ሚሊየን ስልኮችን ሸጠ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 24፣ 2011 (ኤፍ ቢሲ) በአሜሪካ መንግስት የታገደው ሁዋዌ በመጀመሪያው የፈረንጆቹ ሩብ ዓመት 59 ነጥብ 1 ሚሊየን ስልኮችን መሸጡ ተነገረ፡፡

ይህ ሽያጭ ባለፈው ዓመት ከነበረው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ50 በመቶ  ብልጫ አለው ተብሏል፡፡

ሁዋዌ በአሜሪካ መታገዱ ለከፍተኛ ኪሳራ እንዳይዳርግ ተሰግቶ የነበረ ቢሆንም በሩብ ዓመቱ ከፍተኛ ሽያጭ ማስመዝገቡ  በሁለት ድርጅቶች የተካሄዱ ጥናቶች አረጋግጠዋል፡፡

በሌላ በኩል የሳምሰንግ እና የአፕል የሩብ አመት ሽያጭ ቅናሽ ማሳየቱ የተነገረ ሲሆን በተለይ የአፕል ሽያጭ በከፍተኛ ሁኔታ መቀነሱ ተነግሯል፡፡

አፕል በሩብ ዓመቱ 15 ነጥብ 8 ሚሊየን ስልኮችን መሸጡ የተነገረ ሲሆን ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር ዝቅተኛ  ነው ተብሏል፡፡

ሆኖም ሌላኛው ጥናት ያካሄደው ድርጅት ሳምሰንግ 12 ነጥብ 2 ሚሊየን ብቻ ስልኮችን በሩብ አመቱ መሸጡን  አስታውቋል፡፡

 

ምንጭ፡- www.cnet.com

You might also like
Comments
Loading...