Fana: At a Speed of Life!

540 ሚሊየን የፌስቡክ መረጃዎች በአማዞን ሰርቨር ላይ እንደሚገኙ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 26፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ከፌስቡክ የተሰበሰቡ 540 ሚሊየን መረጃዎች በኦንላይ ህዝብ የመረጃ ቋት ላይ እንደሚገኝ አፕጋርድ የተሰኘ የደህንነት ጥናት ተቋም አስታወቀ፡፡

እነዚህ መረጃዎች የሰዎች አስተያየቶችን፣ ላይኮችን፣ የተጠቃሚ ስሞችን እና የፌስቡክ መለያዎችን ያካተተ ነው የተባለ ሲሆን፥ ይህም በሁለት ሶስተኛ የፌስቡክ መተግበሪያዎች የተሰበሰበ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

የፌስቡክ ፓሊሲ መረጃዎች በህዝብ የመረጃ ቋት እንዲሰበሰቡ የማይፈቅድ ሲሆን፥ አማዞን መረጃውን እንዲያነሳ እየሰራ መሆኑን አስታውቋል፡፡

ፌስቡክ ከአበልፃጊዎች ጋር በመሆን የደንበኞቻቸውን መረጃ ለመጠበቅ የሚያስችል ስርዓት ለመዘርጋት እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ነው ይፋ ያደረገው፡፡

ይህ በአማዞን ሰርቨር ላይ የተገኘው መረጃ ምንም አይነት ጥበቃ የማይደረግለት እንደነበረ ተነግሯል፡፡

የደህንነት ጥናት ተቋማት አማዞን የመረጃ ቋቱን ደህንነት እንዲያረጋግጥ ጥሪ ያቀረቡ ቢሆንም ኩባንያው ምንም አይነት እርምጃ እንዳልወሰደ ተነግሯል፡፡

ምንጭ፡-cnet

You might also like
Comments
Loading...