Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል ኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር 33 የሸኔ አባላትን ጨምሮ 145 ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ዋሉ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) 33 የሸኔ አባላትን ጨምሮ 145 ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር ዞን አስታወቀ፡፡

በኦሮሞ ብሄረሰብ አሥተዳደር እየተካሄደ ባለው ህግ የማስከበር እርምጃ በወንጀል የተጠረጠሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር እየዋሉ መሆናቸውን ዋና አስተዳዳሪው አቶ አህመድ አሊ ገልጸዋል፡፡

ዋና አስተዳዳሪው በሰጡት መግለጫ ÷ኅብረተሰቡ የህግ የበላይነት አልተከበርም የሚል ጥያቄ ሲያነሳ መቆየቱን ገልጸው፤ በሳምንት ውስጥ በተከናወነው ስራ 33 የኦነግ ሸኔ አባላትን ጨምሮ 145 ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር  ስር መዋላቸውን ተናግረዋል፡፡

ተጠርጣሪዎችን ለይቶ ለህግ ለማቅረብ ከኅብረተሰቡ ጋር በጋራ እየተሠራ መሆኑን ጠቅሰው÷ በዚህም በዞኑ አንጻራዊ ሰላም መስፈኑን ነው የጠቆሙት።

በህግ ማስከበር ዘመቻው ንፁሃን ያለአግባብ እንዳይያዙ በጥንቃቄ እየተሰራ እንደሚገኝም ዋና አስተዳዳሪው አስታውቀዋል።

የተጀመረው የህግ ማስከበር ተግባር ይበልጥ ውጤታማ እንዲሆን ከአጎራባች ዞኖችና ክልሎች ጋር በቅንጅት እየተሰራ እንደሆነ መናገራቸውንም አሚኮ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.