Fana: At a Speed of Life!

ፑቲን ኪም የኒውክሌር ፕሮግራማቸውን ለመቋረጥ የደህንነት ዋስትና እንደሚያስፈልጋቸው ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 17፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን የሰሜን ኮሪያው አቻቸው ኪም ጆንግ ኡን የኒውክሌር ፕሮግራማቸውን ለመቋረጥ የደህንነት ዋስትና እንደሚያስፈልጋቸው ገለጹ፡፡

የሰሜን ኮሪያው ፕሬዚዳንት ኪም ጆንግ ኡን የኒውክሌር ፕሮግራማቸውን የሚቋርጡ ከሆነ ዓለም አቀፉ የደህንነት ዋስታና ሊሰጣቸው እንደሚገባም ነው ፑቲን የገለጹት፡፡

ፑቲን ኪም የኒውክሌር ፕሮግራማቸውን የሚያቋርጡ ከሆነ ዓለም አቀፉ የደህንነት ዋስትና እንደሚያስፈልጋቸው የገለጹት÷ ሁለቱ መሪዎች በሩሲያ ምስራቃዊ የወደብ ከተማ በሆነችው ቭላዲቮስቶክ አቅራቢያ በሚገኝ ረስኪ በተሰኘ ቦታ በትናንትናው ዕለት ተገናኝተው በመከሩበት ወቅት ነው ተብሏል፡፡

ለሰሜን ኮሪያ ሊሰጣት የመገባው የደህንነት ዋስትናም ዘርፈ ብዙ ጉዳዮችን ሊካትት እንደደሚገባም አመላክተዋል፡፡

በዚሁ ግንኙነታቸው ሁለቱ መሪዎች ጠቃሚ ሃሰቦችን አንስተው መወያየታቸውን አስረድተዋል፡፡

ኪም ጆንግ ኡን በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ግልጽና ነፃ ውይይቶችን ማድረጋቸውንም ፑቲን አንስተዋል፡፡

በዚሁ ውይይት ወቅትም ፑቲን የዓለም አቀፍ ህጉ በሚፈቅደው መሰረት የኮሪያ ልሳነ ምድር ከኒውክሌር የጦር መሳሪያ ነፃ እንዲሆን ፍላጎታቸውን መሆኑንም ለፕሬዚዳንት ኪም ገልጸውላቸዋል ነው የተባለው፡፡

ፕሬዚዳንትትራምፕና የሰሜን ኮሪው አቻቸው በቬትናም ሃኖይ ተገናኝተው በሰሜን ኮሪያ የኒውክሌርና የኢኮኖሚ ማዕቀብ ጉዳዮች ዙሪያ ያለአንዳች ስምምነት መለያየታቸው ይታወሳል፡፡

ምንጭ፡- ቢ ቢ ሲ

You might also like
Comments
Loading...