Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዶክተር አብይ አሕመድ ከኢቫንካ ትራምፕ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 7 ፣ 2011 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አሕመድ ከአሜሪካው ፕሬዚዳንት ልጅ እና አማካሪ ኢቫንካ ትራምፕ ጋር ተወያዩ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኢቫንካ ትራምፕ ከሚመራው ልዑክ ጋር በጋራ ጉዳዮች ላይ ውይይት ማድረጋቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ኢቫንካ ትራምፕ ኢትዮጵያ የገቡት አሜሪካ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሴቶችን ኢኮኖሚያዊ አቅም ለማጎልበት ካቀደችው የሴቶች ዓለም አቀፍ ልማት እና ብልጽግና ፕሮግራም ጋር ተያይዞ ነው።

አማካሪዋ በዛሬው እለት ከኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ጋር ተወያይተዋል።

ከዚህ ባለፈም ጠዋት ላይ በቅድስት ስላሴ ካቴድራል ቤተ ክርስቲያን በመገኘት በቦይንግ የአውሮፕላን አደጋ ህይዎታቸውን ላጡ ዜጎች የአበባ ጉንጉን አስቀምጠዋል።

የኢትዮጵያ ቆይታቸውን ካጠናቀቁ በኋላም ወደ አይቮሪኮስት የሚያቀኑ ይሆናል።

You might also like
Comments
Loading...