Fana: At a Speed of Life!

የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ ከደንቢ ዶሎ ነዋሪዎች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 11፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ከቄለም ወለጋ ዞን ከተውጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች እና ከደንቢ ዶሎ ነዋሪዎች ጋር ተወያዩ ፡፡

በዚህ ወቅት  የኦሮሞ ህዝብ መሰረታዊ የፖለቲካ ጥያቄን  ለዘለቄታው ለመመለስ በትጋት እንደሚሰራ ነው የተናገሩት፡፡

በክልሉ አልፎ አልፎ የሚስተዋለውን የሰላም ችግር በቀጣይ ፖለቲካዊ ትግል በመፍታት የህዝባችንን ዘላቂ ሰላም እናረጋግጣለንም ብለዋል፡፡

በዚህ ውይይት የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ፓርቲ (ኦዲፒ) ማዕከላዊ ኮሚቴ ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ አዲሱ አረጋ ተሳታፊ ሆነዋል፡፡።

ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ አቶ ሽመልስ እና አቶ አዲሱ በዛሬው ዕለት ደንቢ ዶሎ ሲደርሱ በዞኑ ከፍተኛ አመራሮች እና ነዋሪዎች አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

በትናንትናው ዕለት የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር በመሆን የተሾሙት አቶ ሽመልስ የመጀመሪያቸውን የህዝብ ውይይት ነው እያካሄዱ የሚገኙት።

You might also like
Comments
Loading...