Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮ-ጀርመን የቴክኖሎጂ ማበልፀጊያ ማዕከል ለመግንባት የሚያስችል ስምምነት ተደረገ

አዲስ አበባ፣ሚያዚያ 7፣2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮ-ጀርመን የቴክኖሎጂ ማበልፀጊያ ማዕከል ለመግንባት የሚያስችል ስምምነት በዛሬው ዕለት ተፈፅሟል።

ስምምነቱንም የኢኖቬሽንና ቴክሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ሹመቴ ግዛውና የባቫሪያን የኢኮኖሚ ጉዳዮች ክልላዊ ልማትና ኢነርጂ ምክትል ሚኒስትር ሮላንድ ዊገርት ተፈራርመውታል።

ማዕከሉ የኢትዮጵያ እና የጀርመን ቴክኖሎጂዎች የሚለሙበትና ወደ ምርት የሚቀየሩበት መሆኑን ከኢኖቬሽንና ቴክሎጂ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ከዚህ ባለፈም በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ዘርፍ የምርምርና የፈጠራ ስራ ያላቸው ወጣቶች ስራዎቻቸውን የሚያዳብሩበትና ወደ ምርት የሚቀይሩበት ገንዘብ እንዲያገኙ የሚያስችል መሆኑ ነው የተገለፀው።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በቴክኖሎጂ ዘርፍ የዳበረ ልምድ ካላቸው ሀገራት ጋር ዘርፉ የስራ እድል እንዲፈጥር ለማድረግ በትብብር እየሰራ ይገኛል።

You might also like
Comments
Loading...