Fana: At a Speed of Life!

የትራንስ ኔሽን ኤርዌይስ ሄሊኮፕተር አደጋ ደረሰበት

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 18፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ባለቤትነቱ የትራንስ ኔሽን ኤርዌይስ ሄሊኮፕተር ከቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ተነስቶ በመብረር ላይ እያላ ቡልቡላ አካባቢ አደጋ ደረሰበት፡፡

ሄሊኮፕተሩ አምስት መንገዶኞችን እና ሁለት አብራሪዎችን ይዞ እንደነበረ ነው ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ያረጋገጠው፡፡

በዚህ አደጋ በመንገደኞችም ሆነ በአብራሪዎች ላይ ጉዳት እንዳልደረሰ የኢትዮጵያ ሲቭል አቪዬሽን ዋና ዳይሬክተር ኮሎኔል ወሰንየለህ ሁነኛው ተናግረዋል፡፡

ይህ ሄሊኮፕተሩ በመኖሪያ ቤት ላይ መውደቁም ተነግሯል፡፡

የአደጋው ምክንያት እና አጠቃላይ በአደጋው የደረሰው ጉዳት እየተጠራ እንደሚገኝ ነው የተናገሩት፡፡

ትራንስ ኔሽን ኤርዌይስ የሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ኩባንያዎች አባል እንደሆነ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

 

 

Photo Credit:- Ethiopian Reporter

 

You might also like
Comments
Loading...