Fana: At a Speed of Life!

የሱዳን ተቃዋሚ መሪዎች ጊዜያዊ የሲቪል  ምክር ቤት ሊያቋቁሙ ነው

አዲስ አበባ፣ሚያዚያ 12፣2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሱዳን ተቃዋሚ መሪዎች ሀገሪቱን በጊዜያዊነት የሚያስተዳድር የሲቪል ምክር ቤት ሊያቋቁሙ ነው።

ሱዳናውያን  በቅርቡ ፕሬዚዳንት አልበሽርን ከስልጣን በማስወገድ ሀገሪቱን እየመራ ያለው  ወታደራዊ የሽግግር ምክር ቤት ስልጣን እንዲለቅ  ጫና ማሳደራቸውን ቀጥለዋል ።

በዚህ መሰረትም ወታደራዊ የሽግግር ምክር ቤቱ ስልጣኑን  በፍጥነት ለሲቪል  አስተዳደር እንዲያስረክብ  እየጠየቁ  ይገኛሉ ።

በትናንትናው ዕለት በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ሱዳንያውያን በመከላከያ ሚኒስቴር ቢሮ ፊት ለፊት በመገኘት ወታደራዊ የሽግርር መንግስቱ በፍጥነት ስልጣኑን ለሲቭል ዜጎች እንዲያስረክብ አሳስበዋል ።

የሱዳን ባለሙያዎች ማህበር ጉዳዩን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ  በነገው ዕለት የውጭ ዲፕሎማቶች በሚገኙበት ስብሰባ  ላይ የሲቭል አስተዳደር ምክር ቤት አባላት የሚመረጡ መሆኑን አስታውቋል።

በዚህ መሰረትም  በነገረው ዕለት ሀገሪቱን በጊዜያዊነት የሚያስተዳድሩ የሲቭል ምክር ቤት አባላትን ይፋ የሚያደርጉ መሆኑ ነው የተገለፀው።

ለሽግግር ምክር ቤቱ  የሚመረጡት አባላትም ከሃኪሞች፣ከመምህራን ከኢንጂነር ማህበሮች የተውጣጡ ተወካዮች ናቸው ተብሏል።

ከሚመረጡት የምክር ቤት አባላት ውስጥም 40 በመቶ የሚሆነው ቦታ ለሴቶች የሚሰጥ መሆኑ ተገልጿል።

 

ምንጭ ፦አልጂዚራ

You might also like
Comments
Loading...