Fana: At a Speed of Life!

የመርካቶና አከባቢዋ ግብር ከፋይዮች በማገገሚያ ማዕከላት ለሚገኙ ዜጎች 16 የቀንድ ከብት ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 17፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ)የመርካቶና አከባቢዋ ግብር ከፋይ ነጋዴዎች የፋሲካ በዓልን ምክንያት በማድረግ በማገገሚያ ማዕከላት ለሚገኙ ዜጎች 16 የቀንድ ከብቶችና የ200 ሺህ ብር ድጋፍ አደረጉ፡፡

የነጋዴዎቹ ተወካዮች በከተማ አስተዳደሩ የተቋቋመውን የማህበራዊ ትረስት ፈንድ በዘላቂነት እንደሚደግፉም ማስታወቃቸውንም ነው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካንቲባ ጽህፍት ቤት መረጃ የሚያመለክተው፡፡

በርክክቡ ስነ ስርዓት ላይ የተገኙት የማህበራዊ ትረስት ፈንዱ የቦርድ አባላትና አመራሮች የመርካቶና አከባቢዋ ግብር ከፋይ ነጋዴዎች ላደረጉት ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

ህብረተሰቡ በማገገሚያ ማዕከላት ላሉ ወገኖቻችን የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥልም ጥሪቸውን አስተላልፈዋል፡፡

You might also like
Comments
Loading...