Fana: At a Speed of Life!

የህፃናት የወባ መከላከያ ክትባት በሙከራ ደረጃ መሰጠት ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 16፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በዓለማችን በአይነቱ የመጀመሪያው ነው የተባለው የህፃናት የወባ መከላከያ ክትባት በሙከራ ደረጃ በማላዊ መሰጠት ተጀመረ።

አር.ቲ.ኤስ.ኤስ የሚል መጠሪያ ያለው ክትባቱ የሰውነታችንን በሽታ የመከላከል ስርዓት የወባ ትንኝ ንክሻ የሚመጣውን የወባ በሽታን መከላከል እንዲችል የሚያለማመድ ተብሏል።

ከዚህ ቀደም በክትባቱ ላይ በተደረገ አነስተኛ ሙከራ ክትባቱን ከ5 ወር እስከ 1 ዓመት ከ5 ወር እድሜ ያላቸው ህፃናት በመውሰድ 40 በመቶ ያክሉ ከወባ በሽታ ተጋላጭነት የተጠበቁ መሆኑ ታውቋል።

የዓለም ጤና ድርጅት የበሽታ መከላከልና ክትባት ዳይሬክተር ዶክተር ኬት ኦበሪን፥ አሁን በሙከራ ደረጃ መሰጠት የተጀመረው ክትባት የወባ በሽታን በማጥፋት እንዲሁም በሽታዎችን በመከላከልና ለአጠቃላይ የህብረተሰብ ጤና ዘፍር ከሚሰሩ ስራዎች ትልቁን ድርሻ የሚይዝ ነው ብለዋል።

ክትባቱ በአሁኑ ወቅት በላማዊ እየተሰጠ ሲሆን፥ ክትባቱን በሙከራ ደረጃ ለመስጠተም ከተመረጡ ሶስት ሀገራት ወስጥ አንዷ መሆኗም ተነግሯል።

በማላዊ ብቻ 120 ሺህ ህፃናትን ከወባ በሽታ ተጋላጭነት መታቀዱም ነው የተነገረው።

ከማላዊ በመቀጠልም የወባ በሽታ መከላከያ ክትባቱን በቀጣዩ ሳምንት ከጋና እና በኬንያ በሙከራ ደረጃ መሰጠት አንደሚጀመር ነው የተገለፀው።

በዓለም ዙሪያ የወባ በሽታ በየዓመቱ 435 ሺህ ሰዎችን ህይወት እንደሚቀጥፍ የተነገረ ሲሆን፥ ከእነዚህም ወስጥ አብዛኛዎቹ ህፃናት መሆናቸውን መረጃዎች ያመለክታሉ።

ምንጭ፦ www.bbc.com

You might also like
Comments
Loading...