Fana: At a Speed of Life!

የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ በኔውዝርላንድ አቻቸው ትሬቨር ማላርድ የተመራ ልኡክን ተቀብለው አነጋገሩ

አዲስ አበባ፣ ሚዚያ 7፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ በኔውዝርላንድ አቻቸውን ትሬቨር ማላርድ የተመራ ልኡክን ተቀብለው አነጋገሩ፡፡

የኒውዝርላንድ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ልኡካን ቡድን ከኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጋር የእርስ በርስ ፓርላመንታዊ ግንኙነቱን ለማጠናከርና የልምድ ልውውጥ ለመቅሰም እንደመጣም ተነግሯል፡፡

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ አሁን ላይ በኢትዮጵያ እየታየ ያለው ለውጥ ግቡን እንዲመታ የሀገራት ድጋፍ እደሚስፍልግ በመግለጽ÷ የኒውዝርላንድ መንግስትም ይህንን ለማድረግ ያሳየውን አጋርነት አድንቀዋል፡፡

የኒውዝርላንድ ባለሀብቶች መዋዕለ ንዋያቸውን በኢትዮጵያ እንዲያፈሱ ለኒውዘር ላንዱ አቻቸው ጥያቄአቸውን አቅርበዋል፡፡

ኢትዮጵያ ከጎረቤት ሀገራት ጋር ያላትን መልካም ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነትና በምስራቅ አፍሪካ ሰላምና መረጋጋትን በዘላቂነት ለማስፈን ቁርጠኛ መሆኗን አፈ ጉባኤው አስረድተዋል፡፡

የኒውዝርላንዱ አቻቸው ትሬቨር ማላርድ በበኩላቸው ኢትዮጵያ እያካሄደች ያለውን ሁለንተናዊ ለውጥ አድንቀው አገራቸው ይህንን ለውጥ እንደምትደግፍ አረጋግጠዋል፡፡

በውይይቱም ወቅት ኢትዮጵያና ኒውዝርላንድ የሁለትዮሽ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር እንደሚሰሩ የሁለቱ አገር አፈጉባኤዎች መክረዋል፡፡

You might also like
Comments
Loading...