Fana: At a Speed of Life!

የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር በስምንት ወራት ውስጥ ያስገባው ገቢ ከእቅዱ አንፃር ዝቅተኛ መሆኑ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 6፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር በ2011 በጀት ዓመት ለመሰብሰብ ካቀደው 1 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ገቢ  በስምንት ወራት ውስጥ 8 37 ሚሊየን ብር መሰብሰቡን የከተማው ገቢዎች ባለስልጣን ዋና ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት አስታወቀ።

በከተማ አስተዳደሩ የተሰበሰበው ገቢ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ81 ነጥብ 9 ሚሊየን ብር ብልጫ እንዳለው ነው የተነገረው፡፡

ሆኖም በበጀት አመቱ ከተያዘው እቅድ አንፃር ግን አፈፃፀሙ ዝቅተኛ እንደሆነ ነው የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ፍቃዱ ፍሰሀ የተናገሩት፡፡

ለገቢው ዝቀተኛ መሆን በከተማዋ በተደጋጋሚ ሲከሰቱ የነበሩ የፀጥታ ችግር እና  ያንን ተከትሎ የተበራከተው የኮንትሮባንድ ንግድ ዋነኛ ምክንያቶች መሆናቸውን ኃላፊው ተናግረዋል።

ይህንን ተከትሎም ጽህፈት ቤቱ በቀጣይ የገቢ አሰባሰቡን እቅድ ለማሳካት እንዲችል ከባለድርሻ ጋር መክሯል።

የተንሰራፋዉን የህገወጥ ንግድ አብሮ በመዋጋት ግብር ከፋዩ የሚጠበቅበትን ግዴታ እንዲወጣም ጥሪ ቀርቧል።

በቀሪ ጊዜያትም የሚታዩትን ችግሮች በታክስ ንቅናቄ ፣ ከንግዱ ማሀበረሰብና ከባለድርሻ  አካላት ጋር ሆኖ በማስወገድ ዕቅዱን ለማሳካት ርብርብ እንደሚደረግ ተነግሯል፡፡

 

በታምራት ቢሻዉ

You might also like
Comments
Loading...