Fana: At a Speed of Life!

ወርቃማው ፍቅር የተባለለት የአዛውንቶቹ ጋብቻ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 25፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ቻይናውያኑ ጥንድ አዛውንቶች በ96 እና በ85 ዓመታቸው ጋብቻ መፈፀማቸው ተሰምቷል።

በቻይናዋ ሁቤይ ግዛት ውሃን ከተማ ባሳለፍነው ሳምንት ጋብቻቸውን የፈፀሙት አዛውንቶቹ የ96 ዓመቱ ሀን እና የ85 ዓመቷ ዉ የሚባሉ ናቸው።

ጥንዶቹ የተዋወቁት እና በፍቅር የወደቁትም በአውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2017 እንደነበረ ነው መረጃዎች የሚጠቁሙት።

ሀን እና ው የተባሉት ጥንዶቹ ከዚህ ቀደም የነበራቸውን የትዳር አጋሮቻቸውን አጥተው በብቸኝነት ነበር ኑሮን በመግፋት ላይ የነበሩት።

እንደ አጋጣሚ ይሆንና የሀን እና ው ልጆች ጓደኛሞች ናቸው፤ ታዲያ ልጆቹ የቤተሰብ ጊዜ አዘጋጅተው አንድ ላይ በሚሰባሰቡበት ጊዜም ለአዛውንቶቹ ጥንዶች የመተዋወቂያ እድል ተፈጠረ።

መጀመሪያውኑ ቤተሰቦቻቸው ብቻቸውን መኖራቸውን ያሳስባቸው የነበሩ ልጆችን ሁለቱን በማቀራረብ እና በጋራ እንዲኖሩ ለማድረግ በመወሰን  አቀራርበዋል።

በዚህ ሁኔታ የተዋወቁትና የተቀራረቡት ጥንዶቹ ባሳለፍነው የፈረንጆቹ 2018 ቀለበት ያሰሩ ሲሆን፥ ባሳለፍነው ሀሙስ ደግሞ የጋብቻ ስነ ስርዓታቸውን ፈፅመዋል።

እድሜ ያልበገረውን የአዛውንቶቹን ጥንዶች ጋብቻ የሰሙ በርካቶችም “ወርቃማው ፍቅር” ሲሉ ገልፀውታል።

ምንጭ፦ www.chinadaily.com.cn

You might also like
Comments
Loading...