Fana: At a Speed of Life!

ከልክ በላይ ለሆነ ወፍረት የተጋለጡ እናቶች የጡት ወተት በህፃናት ክብደት ላይ ተፅዕኖ እንዳለው ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 3፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) እናቶች ጤናማ ወይንም ከልክ በላይ ወፍረት ይኑራቸው በከፍተኛ ሁኔታ በህፃናት  ሰውነት ላይ ተፅእኖ እንደሚኖረው ይገለፅ ነበር፡፡

አሁን ይፋ የሆነው አዲስ ጥናትም ከዚህ ጋር የሚቀራረብ ውጤት ይፋ ማድረጉ ተነግሯል፡፡

ጥናቱ ከልክ በላይ የሰውነት ክብደት ባላቸው እናቶች  የጡት ወተት የሚገኘው የሞሎኪውል  ጤናማ ሰውነት ካላቸው እናቶች የተለየ መሆኑ ነው የተነገረው፡፡

ይህም የህፃናትን የሰውነት ክብደት  ላይ ተፅዕኖ እንደሚኖረው አዲሱ ጥናት ይፋ አድርጓል፡፡

ተመራማሪዎቹ ከልክ ያለፈ ክብደት እና ጤናማ ክብደት ያላቸው እናቶች  በህፃናት የሰውነት ክብደት ላይ ተፅዕኖ  የሚያሳድረው ሜታቦሊቴዎች  እንዳሏቸው አረጋግጠዋል፡፡

ከልክ ያለፈ ክብደት ያላቸው ህፃናት ለስኳር በሽታና ለሌሎች በሽታዎች የመጋለጥ እድላቸው ከፍተኛ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን የጥናቱ ዋና አላማም ህፃናት ከልክ ባለፈ ክብደት ምክንያት ሊያጋጥሟቸው የሚችሉ አደጋዎችን ለማወቅ የተካሄደ ነው ተብሏል፡፡

ምንጭ፡-upi

You might also like
Comments
Loading...