Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያና ደቡብ ኮሪያ የ264 ሚሊየን ዶላር የቀላል ብድር ስምምነት ተፈራረሙ  

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 14 ፣ 2011 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያና ደቡብ ኮሪያ የ264 ሚሊየን ዶላር ቀላል ብድር ማቅረብ የሚያስችል የማዕቀፍ ስምምነት ተፈራረሙ።

ስምምነቱ በኢትዮጵያ ውስጥ ለሚከናወኑ የልማት ፕሮክቶች የሚውል ሲሆን፥ የደቡብ ኮሪያ ኤክስፖርትና ኢምፖርት ባንክ እና የገንዘብ ሚኒስቴር ተፈራርመውታል።

የመጀመሪያው የ170 ሚሊየን ዶላር የብድር ስምምነት በደቡብ ኢትዮጵያ ለሚገኘው የብሔራዊ የኤሌክትሪክ ኃይል ፍሰትና የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ ፕሮጀክት የሚውል መሆኑ በስምምነቱ ወቅት ተገልጿል።

በዚህም በኢትዮጵያ በሰሜን ምዕራብ ለሚገኙ የሀገሪቱ ክፍሎችና እና ለኦሞ ስኳር ፋብሪካ ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ሀይል ለማቅረብ ያስችላል ተብሏል፡

በተጨማሪም ለአርባምንጭ ኢንዱስትሪያል ፓርክ ግንባታም ይውላል መባሉን ከገንዘብ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ሁለተኛውና የ94 ሚሊየን ዶላር የቀላል ብድር ስምምነቱ ደግሞ በሀገሪቱ ውስጥ ለሚሰሩ የመስኖ ልማትና የገጠር ልማት ፕሮጀክቶች እንደሚውል ተጠቅሷል፡፡

በዚህም አርሶ አደሩ የግብርና ምርቱን እንዲያሳድግና ገቢው እንዲጨምር ያደርጋል ተብሏል።

 

 

 

You might also like
Comments
Loading...