Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያና ሩዋንዳ በወጣቶች ልማት ዘርፍ በትብብር ለመስራት ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 15፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኢትዮጵያና ሩዋንዳ በወጣቶች ልማት ዘርፍ በትብብርና በቅንጅት ለመስራት ተስማምተዋል።

የኢፌዴሪ የሴቶች፣ህጻናትና ወጣቶች ጉዳይ ሚኒስትር ወይዘሮ ያለም ጸጋዬ ከሩዋንዳ አቻቸው ሮዝሜሪ ምባዚ ጋር በዛሬው ዕለት በኪጋሊ ተወያይተዋል።

በውይታቸውም ኢትዮጵያና ሩዋንዳ በወጣቶች ልማት ዘርፍ ያላቸውን ተሞክሮ ለመካፈልና ለመተባበር መስማማታቸው ነው የተገለፀው።

ከዚህ ባለፈም ሚኒስትሮቹ የሁለቱን ወዳጅ ሀገራት ግንኙነት በሁሉም መስኮች ለማጠናከር በቅንጅት መስራት እንደሚገባ ማሳሰባቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

You might also like
Comments
Loading...