Fana: At a Speed of Life!

ኢራንና ፓኪስታን ሽብርተኝነትን በጋራ ለመከላከል ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 15፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኢራንና ፓኪስታን በቀጠናው የሚስተዋለውን የሽብር ድርጊት በጋራ ለመከላከል መስማማታቸው ተነግሯል።

ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ቴህራን የሚገኙት የፓኪስታን ጠቅላይ ሚኒስትር ኢምራን ካህን በትናንትናው ዕለት ከኢራን ፕሬዚዳንት ሀሰን ሩሃኒ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል።

ሀሰን ሩሃኒ ውይይታቸው  አስመልክተው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፥ ሁለቱ ሀገራት በቀጠናው የሚስተዋለውን የሽብር ድርጊት በጋራና በቅንጅት ለመከላከል መስማማታቸውን ተናግረዋል።

በዚህ መሰረትም ቴህራንና እስላማባድ በአካባቢው የሚፈጸመውን የሽብር ጥቃት ለመከላከል ብሎም ለማስወገድ የሚያስችል የጋራ ጥምር ሃይል ለማቋቋም ስምምነት ላይ ደርሰዋል ነው ያሉት ።

የሚቋቋመው የጋራ ጥምር ሃይልም በሀገራቱ ድንበሮች አካባቢ ያለውን የፀጥታና ደህንነት ጉዳይ በቅንጅትና  በትኩረት የሚቆጣጠር ነው ተብሏል።

ይህም በኢራን ጠላት ሀገራት የሚደገፉና በቀጠናው የሚንቀሳቀሱ የሽብር ቡድኖች የሚፈፅሙትን ዕኩይ ድርጊት  ለማክሸፍ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል ብለዋል በመግለጫቸው።

ከዚህ ባለፈም የኢራንና የፓኪስታን ግንኙነት መጠናከር በቀጠናው  አለመረጋጋትንና ቀውስን ለመፍጠር ብሎም የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ለማሻከር የሚሰሩ አካላትን ያሳፈረ ነው ብለዋል።

ምንጭ ፦presstv.com

 

You might also like
Comments
Loading...