Fana: At a Speed of Life!

ባየር ሙኒክ ለፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ስማቸው ያረፈበትን ማልያ አበረከተ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 9 ፣ 2011 (ኤፍ ቢ ሲ) የጀርመኑ ባየር ሙኒክ እግር ኳስ ክለብ ለፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ስማቸው ያረፈበት የክለቡን ማልያ በስጦታነት አበርክቷል።

የባቫሪያን ግዛት ሚኒስትር – ፕሬዚዳንት ማርከስ ሶደርም ለፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ፥ ከጀርባው 1 ቁጥር የተጻፈበትንና የፕሬዚዳንቷ ስም ያረፈበትን ማልያ አበርክተውላቸዋል።

የጀርመኑ ሃያል ክለብ በስሙ የሚጠራውን እና በአፍሪካ የመጀመሪያው የሆነውን የእግር ኳስ ማሰልጠኛ በአዲስ አበባ ይከፍታል።

በኢትዮጵያ የሚከፈተው የእግር ኳስ ማሰልጠኛም ክለቡ አለም ላይ የከፈታቸውን ተመሳሳይ የእግር ኳስ ማሰልጠኛ ተቋማቱን ስድስት እንደሚያደርሰው ከፕሬዚዳንት ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ቀደም ሲል ክለቡ በአሜሪካ፣ ቻይና፣ ታይላንድ፣ ጃፓን እና ሲንጋፖር እግር ኳስ ማሰልጠኛዎችን ከፍቷል።

 

You might also like
Comments
Loading...