Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 22ኛ ሳምንት ጨዋታ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 22፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ)የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 22ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በዛሬው እለት ተካሂደዋል።

በተደረጉ ጨዋታዎችም በአዳማ አበበ ቢቂላ ስታዲየም አዳማ ከተማ ኢትጵያ ቡናን አስተናግዶ 1 ለ 0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

አዳማ ከተማ ከኢትዮጵያ ቡና ሶስት ነጥብ እንዲያገኝ ያስቻለችውን ግብ ዱላ ሙላቱ በ74ኛው ደቂቃ ላይ ነው ያስቆጠረው።

በፕሪምየር ሊጉ በሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ፋሲል ከነማ ድሬደዋ ከተማን አስተናግዶ 2ለ0 ማሸነፍ ችሏል።

የፋሲል ከነማን የማሸነፊያ ግቦች ሙጂብ ቃሲም በ7ኛው ደቂቃ እና ኤፍሬም አለሙ በ14 ኛው ደቂቃ ላይ አስቆጥረዋል።

ወልዋሎ አዲግራት የኒቨርስቲ ወራጅ ቀጠና የሚገኘውን ደደቢትን አስተናግዶ 2ለ ያሸነፈ ሲሆን ግቦቹን ኤፍሬም አሻሞ በ3ኛ እና ሪችሞንድ አዶንጎ በ44ኛ ደቂቃ ላይ ነው ያስቆጠሩት።

በሌላ ጨዋታ በ16 ነጥብ ወራጅ ቀጣና ላይ የሚገኘው ስሑል ሽረ ሀዋሳ ከተማን በሰፊ የግብ ልዩነት 4 ለ 0 ማሸነፍ ያቻለ ሲሆን ግቦቹን ቢስማርክ አፒያ እና ቢስማርክ ኦፖንግ አንድንድ ግቦችን ሲያስቆጥሩ ሳሊፍ ፎፋና ሁለት ግቦችን አስቆሯል።

ጅማ አባ ጅፋር በሶስተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘውን ሲዳማ ቡና አስተናግዶ ኦኪኪ አፎላቢ በ47ኛው ደቂቃ ላይ ባስቆጠረው ብቸኛ ግብ 1 ለ 0 አሸንፏል።

ባህርዳር ከደቡብ ፓሊስ ያደረጉት ሌላኛው ጨዋታ 3 አቻ በሆነ ውጤት ነው የተጠናቀቀው።

በአዲስ አበባ ስታዲየም ቅዱስ ጊዮርጊስን ከመሪው መቐለ 70 እንደርታ ያገናኘው ጨዋታ ደግሞ በቅዱስ ጊዮርጊስ 1ለ0 አሸናፊነት ተጠናቋል።

የቅዱስ ጊዮርጊስን ብቸኛ የማሸነፊያ ጎልም አስቻለው ታመነ በፍፁም ቅጣት ምት ከመረብ አሳርፏል።

You might also like
Comments
Loading...