Fana: At a Speed of Life!

በጀርባቸው የሚተኙ እርጉዝ እናቶች ያላቀናቸው የመወለድ እድላቸው ከፍተኛ ነው  – ጥናት

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 1፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በጀርባቸው የሚተኙ እርጉዝ እናቶች ያለቀናቸው የመውለድ እድላቸው ከፍተኛ መሆኑን አንድ ጥናት አመለከተ፡፡

የኒውዚላንድ ተማራማሪዎች በአውስትራሊያ፣ ብሪታኒያና አሜሪካ እናቶች ላይ ባደረጉት ጥናት ከጸነሱ በኋላ በጀርባቸው የሚተኙ እናቶች ካለቀናቸው የመውለድ እድላቸው ከፍተኛ መሆኑን አመልክቷል፡፡

በተለይም ጽንሱ 28 ሳምንት ከሆነው በኋላ እናቶች ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባቸው የጥናቱ መሪ ጸሃፊ ተናግረዋል፡፡

በጀርባቸው የመተኛት ልምድ ያላቸው እናቶችም በሚጸንሱበት ወቅት በጎናቸው ተስተካክለው የመተኛት ልምድ ቢያዳብሩ ለእናቶችና ለጽንሱ ጤና ጠቃሚ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ምንጭ- ዩ ፒ አይ

You might also like
Comments
Loading...