Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሰባት ጨዋታዎች ተካሂደው ስድስቱ በመሸናነፍ ተጠናቀቁ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 6፣ 2011 (ኤፍ ቢ ሲ) በዛሬው ዕለት በተካሄዱ 20ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሰባት ጨዋታዎች  ስድስቱ ጨዋታዎች በመሸናነፍ ሲጠናቀቁ አንዱ ጨዋታ በአቻ ውጤት ተጠናቀቀ፡፡

የፕሪምየር ሊጉ መሪ መቐለ 70 እንደርታ በባህርዳር ከነማ 1 ለ 0 በመሸነፍ ከተካታዮቹ ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ማጥበብ ሳይችል ቀርቷል፡፡

በርካታ ተመልካቾች በተከታተሉት በዚህ ጨዋታ ለባህርዳር ከተማ ወሳኛ ሶስት ነጥብ ያስገኘችውን ግብ ሳላምላክ ተገኝ በ22ኛው ደቂቃ ላይ ነው ያስቆጠረው፡፡

ቅዱስ ጊዮርጊስ ሲዳማ ቡናን በአዲስ አበባ ስታድየም አስተናግዶ 2 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡

በጨዋታው የቅዱስ ጊዮርጊስን ግቦች  ኢሱፍ ቡርሀና 35ኛው ደቂቃ እና አቡበከር ሳኒ በ83ኛው ደቂቃ ላይ አስቆጥረዋል፡፡

ወላይታ ድቻ ከኢትዮጵያ ቡና ያደረጉት ተጠባቂ ጨዋታ በወላይታ ድቻ 2 ለ 1 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡

የወላይታን የማሸነፊያ ግቦች ፀጋየ አበራ በ34ና በ79ኛው ደቂቃዎች ሲያስቆጥር ቡናዎችን ከሽንፈት ያልታደገቻቸውን ብቸኛ ግብ  አልሀሰን ካሉሻ በ56ኛው ደቂቃ ላይ አስቆጥሯል፡፡

አዳማ ከተማ ሀዋሳ ከተማን በአበበ ቢቂላ ስታድየም አስተናግዶ 2 ለ 1 በሆነ ውጤት ተሸንፏል፡፡

የሀዋሳ ከተማን ሁለት ግቦች ምንተስኖት አበራ 9ኛው እና  ደስታ ዩሐንስ በ68ኛው ደቂቃ ላይ ሲያስቆጥር የአዳማን ብቸኛ ግብ ቡልቻ ሹራ በ90ኛው ደቂቃ ላይ አስቆጥሯል፡፡

ጅማ አባ ጅፋር ኦኪኪ አፎላቢ 33ኛው እና በአስቻለው ግርማ 60ኛው ደቂቃ ግቦች ወረጅ ቀጠና ውስጥ የሚገኘውን ስሑል ሽረ 2 ለ 0 አሸንፏል፡፡

በሌላ ጨዋታ ጎንደር ፋሲለ ደስ ስታድየም ላይ ደቡብ ፓሊስ ያስተናገደው ፋሲል ከነማ 1 አቻ በሆነ ውጤት ተለያይቷል፡፡

እንዲሁም ደደቢት በሜዳው በድሬደዋ ከተማ 3 ለ 2 በሆነ ውጤት ሽንፈትን አስተናግዷል፡፡

የድሬደዋን ግቦች  ዘነበ ከበደ በ12ኛው  ረመዳን ናስር በ44ኛው እና ፍሬድ ሙሸንዲ በ74ኛው ደቂቃ ላይ ማስቆጠር የቻሉ ሲሆን የደደቢትን ግቦች  የዓብስራ ተስፋዬ በፍፁም ቅጣት ምት በ67ኛውና  መሀድኔ ታደሰ በ88ኛው ደቂቃ ላይ አስቆጥረዋል፡፡

 

You might also like
Comments
Loading...