Fana: At a Speed of Life!

በተለያዩ ከተሞች የፅዳት ዘመቻ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 6 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ከማለዳ ጀምሮ በሀገሪቱ የተለያዩ ከተሞች፣ መንገዶች እና ሰፈሮች የፅዳት ዘመቻ ተካሄደ።

ከጠዋት 1 ሰዓት ከ30 ጀምሮ በተካሄደው የፅዳት መርሃ ግብር በአዲስ አበባ ከተማ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድና ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ተሳትፈዋል፡፡

የጠቅላይ ሚኒስቴር ፅህፈት ቤት እለቱን አስመልክቶ ባስተላለፈው መልክዕክት የምናጸዳው በክብርና በንጹሕ አከባቢ መኖር መብታችን እንደሆነ ስለምናምን ነው ብሏል።

ፅህፈት ቤቱ የምናጸዳው ለጤናችን ነው፤ ማጽዳትም ኃላፊነታችን ነውም ብሏል።

ለኢትዮጵያ ጽዳት በአንድነት እንነሳ በማለት ጥሪ ያስተላለፈው ፅህፈት ቤቱ ሁሉም ኢትዮጵያዊያን ለአካባቢ ፅዳት በአንድነት መነሳት እንዳለባቸው ጠቁሟል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የፅዳት ዘመቻው መልካም አስተሳሰብን ለመስበክ እንደሚያግዝ ማስታወቃቸው የሚታወስ ነው፡

Photo Credit: Office of the Prime Minister-Ethiopia

You might also like
Comments
Loading...