Fana: At a Speed of Life!

በሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ የተነሣውን እሳት ለማጥፋት ሄሊኮፕተሮችና ባለሙያዎች ዝግጅታቸውን አጠናቀዋል

አዲስ አበባ፣ሚያዚያ 5 ፣2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ የተነሣውን እሳት ለማጥፋት የእሳት አደጋ ሄሊኮፕተሮችና የቴክኒክ ባለሙያዎች ዝግጅታቸውን ማጠናቀቃቸውን የጠቅላይ ሚኒስቴር ፅህፈት ቤት ገለፀ።

ከሳምንታት በፊት በሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ የተነሣውን እሳት ለማጥፋት በፌዴራል መንግሥት ደረጃ የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ ባለሥልጣን ከአማራ ክልላዊ መንግሥት ጋር ሲተባበሩ መቆየታቸውን ገልጿል።

ይኸውም የእሳት ማጥፋት ስራው ከዉጭ የእሳት አደጋ ሄሊኮፕተሮች የፌዴራል መንግስት በማስመጣት ላይ በነበረት ግዜ በሀገር ሰው ርብርብ እሳቱን ለማቆም ተችሎ  እንደነበርም አስታውሷል።

በአሁኑ ወቅትም እስካውቶች፣ ልዩ ሕይል አባላትና በጎ ፈቃደኞች ሲረባረቡ ቆይተው ከረቡዕብ ወዲህ ግን እሳቱ በሰው ለመድረስ ከማይቻልበት ረባዳ ቦታ መግባቱን ነው ፅህፈት ቤቱ ያስታወቀው

በመሆኑም በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አመቻችነት የፌዴራልና የክልሉ መንግስት አካላት ባደረጉት ጥረትና ጥሪ ከዉጪ ሀገሮች የተገኙ የእሳት አደጋ ሄሊኮፕተሮች እና የቴክኒክ ባለሙያዎች የእሳት ማጥፋት ሥራውን ለመጀመር ዝግጅታቸውን መጨረሳቸውን ገልጿል።

You might also like
Comments
Loading...