Fana: At a Speed of Life!

በመጭው ዓመት በኢትዮጵያ ለ3 ሚሊየን ዜጎች የስራ እድል መፍጠር እንደሚያስፈልግ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 4፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ብሔራዊ የሥራ እድል ፈጠራ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባውን እያካሄደ ነው።

ምክር ቤቱ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በተገኙበት የበጀት ዓመቱን የዘጠኝ ወር የስራ ፈጠራ እቅድ እና አፈፃፀም ለምክር ቤቱ አባላት አቅርቧል፡፡

በዘጠኝ ወራቱ በከተሞች ለ1 ነጥብ 4 ሚሊየን ዜጎች የስራ እድል ለመፍጠር ታቅዶ ለ1 ሚሊየን ዜጎች የስራ እድል እንደተፈጠረ ገልጿል።

በተመሳሳይ በሀገሪቱ ገጠራማ አካባቢዎች ለ1 ነጥብ 7 ሚሊየን ዜጎች የስራ እል ለመፍጠር ታቅዶ ቢሰራም የስራ እድል መፍጠር የተቻለው ለ1 ነጥብ 08 ሚሊየን ዜጎች መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

ይህም በእቅድ ደረጃ ከተያዘው አንፃር ዝቅተኛ እንደሆነ ነው የተጠቆመው፡፡
በ2012 በጀት አመት በስራ እድል ፈጠራ ዙሪያ ሊሰሩ በሚችል ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል፡፡

በውይይቱም በበጀት ዓመቱ በስራ እድል ፈጠራ ላይ ያሉ ችግሮችን በመቅረፍ ለ3 ሚሊየን ዜጎች የስራ እድል መፍጠር እንደሚገባ ኮሚቴው አስታውቋል፡፡

ችግሩን በመቅረፍ ለዜጎች የስራ እድል ለመፍጠር ብሔራዊ የሥራ እድል ፈጠራ ምክር ቤት የአደረጃጀት እና አሰራር መመሪያ አዘጋጅቷል።

በሀይለየሱስ ስዩም

You might also like
Comments
Loading...