Fana: At a Speed of Life!

5 ነጥብ 5 ሜትር የሚረዝመው የአዛውንቱ ፀጉር

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 24፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በደቡብ ምዕራብ ቻይና ሲቹአን ግዛት ነዋሪ የሆኑት የ77 ዓመት አዛውንት ባለፉት 54 ዓመታት ጸጉራቸውን በመንከባከብ 5 ነጥብ 5 ሜትር ርዝማት እንዲኖረው ማድረጋቸው ተነግሯል፡፡

አዛውንቱ ይህንን ጸጉራቸውን ጸጉር ቤት ሲያሳጥቡ በልጅ ልጃቸው የተወሰደ ምስል በሀገሪቱ ማህበራዊ ሚዲያ ከተለቀቀ በኋላ ጉዳዩ የድጋፍ የትችት አስተያየቶችን እያስተናገደ ይገኛልም ተብሏል፡፡

መረጃው በማህበራዊ ሚዲያ በተለቀቀ በሁለት ቀናት ብቻ 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ተመልካቾችን ማስተናገዱም ተገልጿል፡፡

ከተመልካቾቹ መካከል በዚህ ደረጃ ጸጉርን ማሳደጉ የተለመደ ባለመሆኑ አዛውንቱ ወዲያውኑ ወደ ጸጉር ቤት ሄደው መስተካከል እንዳለባቸው ሲገልጹ÷ ሌሎቹ በዚሁ ተግባራቸው እንዲቀጥሉ በማበረታታት በዓለም ክብረ ወሰን መዝግብ መመዝገብ እንዳለባቸው አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

አኬ ዪዝሀንግ የተባሉት የ77 ዓመት አዛውንት ጸጉራቸው ይህን ያህል ቢያድግም ጠቅልለው እራሳቸው ላይ በማስቀመጥ የሚፈልጉትን ማናቸውንም እንቅስቃሴ እንደሚያደርጉና ስራቸውን ለመከወን ምንም ተጽህኖ እንዳላደረሰባቸው  ነው የተነገረው፡፡

ለዝና እና ክብር ጸጉራቸውን እንዳላሰደጉት የተናገሩት አዛውንቱ በዓለም ክብረ ወሰን መዝገብ ለማስመዝገብ ከአስተያየት ሰጪዎች የቀረበላቸውን ሀሳብ አልተቀበሉም ተብሏል፡፡

የጸጉራቸው አለመስተካከል ለእርሳቸውና ለቤተሰባቸው ጤና ጠቃሚ ነው ከሚል እምነት ጋር በተያያዘ ከ23 ዓመታቸው ጀምሮ ተስተካክለውት እንማያቁም  ተነግሯል፡፡

አዛውንቱ ይህንን ጸጉራቸውን ከወር ሁለት ጊዜ ያህል ጸጉር ቤት ሄደው የሚታጠቡት ሲሆን÷ ለማጠብ፣ ለማጽዳጽትና ለማድረቅ ለሁለት ወይንም ሶስት የጸጉር ቤት ሰራተኞች ሶስት ሰዓት እንደሚፈጅም ዘገባው ያስረዳል፡፡

ምንጭ፡- odditycentral.com

 

 

You might also like
Comments
Loading...