Fana: At a Speed of Life!

ሀገር አቀፍ የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ኤግዚቢሽንና ባዛር የፊታችን ሰኞ ይከፈታል

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 11፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ለ6 ቀናት የሚቆየው ሀገር አቀፍ የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ኤግዚቢሽንና ባዛር የፊታችን ሰኞ በአዲስ አበባ ከተማ ይከፈታል፡፡

ባዛርና ኤግዚቪዥኑ ለ2ኛ ጊዜ የሚካሄድ ሲሆን÷ከሁሉም ክልሎች የተውጣጡ 185 የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ፣10 አነስተኛና መካከለኛ ኢንደስትሪዎች ተሳታፊ እንደሚሆኑ የፌደራል የከተሞች የስራ ዕድል ፈጠራና የምግብ ዋስትና ኤጀንሲ ዛሬ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል፡፡

በማኑፋክቸሪንግ፣ በአግሮፕሮሰሲንግ ፣በዕደጥበብ፣ በቴክኖሎጂ ፈጠራ እና በምርት ዲዛይን ስራ ላይ የተሰማሩ አምራችና ጥቃቅን ኢንተርፕራይዞች ይሳተፉበታል ተብሏል፡፡

ከተሳታፊዎቹ 50 በመቶ ያህሉ ኢንተርፕራይዞች በሴቶች ባለቤትነት የሚንቀሳቀሱ ናቸው፡፡

በያዝነው በጀት አመት ብቻ 14 ሺህ 804 ኢንተርፕራይዞችን ወደ አነስተኛ ደረጃ፣549 ኢንተርፕራይዞችን ወደ መካከለኛ ደረጃ መሸጋገቸውም በመግለጫ ተጠቅሷል፡፡

ባለፉት ሶስት ዓመት ተኩል በመደበኛና በግዙፍ ፕሮጀክቶች ውስጥ ለ6ነጥብ7 ሚሊየን ዜጎች የስራ ዕድል መፍጠር መቻሉም ነው የተገለጸው፡፡

በ1ኛው ዙር ሀገር አቀፍ ኤግዚብሽንና ባዛር ከሽያጭና ከገበያ ትስስር3 ሚሊየን 550 ብር መገኘቱንም ነው የፌደራል የከተሞች የስራ ዕድል ፈጠራና የምግብ ዋስትና ኤጀንሲ ያስታወቀው፡፡

በዘቢብ ተክላይ

You might also like
Comments
Loading...