Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ከፈረንሳይ ከፍተኛ የቢዝነስ ልዑካን ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 6፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ከፈረንሳይ ከፍተኛ የቢዝነስ ልዑኩ ጋር ተወያዩ፡፡

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ለሀገር ውስጥም ለውጭውም ኢንቨስተር አመቺ የሆነ የኢንቨስትመንት መሰረተ ልማት እና አሰራር ለመዘርጋት መንግስት ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

በቢዝነስ ልዑካኑ በበኩላቸው ኢትዮዮጵያ ውስጥ ያለው ዘርፈ ብዙ የኢንቨስትመንት እድል በስፋት ለመሳተፍ ምክንያት እንደሆናቸው ነው ተናገሩት፡፡

የቢዝነስ ልዑካኑ 20 ከሚሆኑ  መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ የፈረንሳይ ተቋማት የተወከሉ ናቸው ተብሏል፡፡

ድርጅቶቹ በሎጅትቲክስ ኔትወርክ፣ በባቡር ቴክኖሎጅ፣ በንፁህ ውሃ አቀርቦት፣ በድጅታል ደህንነት መሳሪያዎች አምራችነት፣ በነዳጅ አቅርቦት፣ በታዳሽ ኃይል እና በመሳሰሉት ዘርፎች የሚሰሩ ዓለም አቀፍ ተቋማት መሆናቸው ተጠቁሟል፡፡

You might also like
Comments
Loading...