Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ በጌዲኦ ተፈናቅለው በመጠለያ ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣መጋቢት 8፣2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ጌዲኦ ዞን ገደብ ወረዳ ተገኝተው ተፈናቅለው በመጠለያ ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን ጎብኝተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ጌዲኦ ዞን ገደብ ወረዳ ወደ ስፍራው የደረሱት ማለዳ ላይ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ በአሁኑ ሰዓት ከጌዲኦ ተፈናቃይ ተወካዮች ጋር ስለሁኔታው በመወያየት ላይ ይገኛሉ።

በውይይቱም በአካባቢው የሚገኙ ተፈናቃዮችም ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ያላቸውን ቅሬታ አቅርበዋል።

ከወራት በፊት ከምዕራብና ምስራቅ ጉጂ እንዲሁም በጌዴኦ ዞን አካባቢዎች በተከሰተ ግጭት በርካታ ዜጎች ከቤት ንብረታቸው መፈናቀላቸውን ይታወሳል።

መንግስትም በጌዴኦ ዞን ለተፈናቀሉ ዜጎች ከለጋሽ ድርጅቶች ጋር በመቀናጀት የአስቸኳይ እርዳታ እያደረሰ እንደሚገኝ በትናትናው ዕለት የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

በሰላማዊት ካሳ

You might also like
Comments
Loading...