Fana: At a Speed of Life!

የሴቶችን ጫና የሚያቃልሉ የቴክኖሎጂ ውጤቶች በቅርቡ ወደ ስራ ሊገቡ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 25፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሴቶችን ጫና የሚያቃልሉ የቴክኖሎጂ ውጤቶች በቅርቡ ወደ ስራ እንደሚገቡ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ሚኒስቴሩ በ7 ክልሎች ውስጥ በቴክኖሎጂ ውጤቶች ሊደገፉ የሚችሉ ሴቶች ላይ ከፍተኛ ጫና እያሳደሩ ያሉ ስራዎችን በጥናት መለየቱን ገልጿል፡፡

በዚህም መሰረት በፀሃይ ሃይል የሚሰራ የምግብ ማብሰያ፣ በሬ ለምኔ ዘመናዊ ማረሻ እና የቆጮ መፋቂያ ማሽን በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ስራ እንደሚገቡ ተገልጿል፡፡

ዘመናዊ የበቆሎ መፈልፈያና የአፋ አሊ (የአፋር ቤት) መስሪያ በመካከለኛ ጊዜ ወደ ስራ ለማስገባት የታቀደ ሲሆን በመስመር መዝሪያ እና ከጉድጓድ ውሃ ማውጫ መሳሪያ ደግሞ በረጅም ጊዜ ወደ ስራ ለማስገባት በእቅድ መያዙንም ሚኒስቴሩ ገልጿል፡፡

ሚኒስቴሩ ለሚመለከታቸው ሁሉ ድጋፋቸውን እንዲያደርጉም ጥሪ ማቅረቡን ከገጹ ላይ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

 

You might also like
Comments
Loading...