Fana: At a Speed of Life!

ኢጋድ በቅርቡ ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ቃል የገባውን የ100 ሺህ ዶላር ቦንድ ግዢ ሊፈጽም ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 15፣ 2011(ኤፍ.ቢ.ሲ) የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት/ኢጋድ/ ከዚህ ቀደም ቃል የገባውን የ100 ሺህ የአሜሪካን ዶላር የታላቁ ህዳሴ ግድብ ቦንድ ግዢ በቅርቡ እንደሚፈጽም አስታወቀ።

ኢጋድ ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ከዚህ ቀደም የ250 ሺህ የአሜሪካን ዶላር ቦንድ ለመግዛት ቃል መግባቱ ይታወሳል።

የድርጅቱ ዋና ጸሃፊ አምባሳደር ማህቡብ ሟሊም እንደገለጹት በኢጋድና በኢትዮጵያ መካከል ያለውን ጠንካራ መስተጋበር አጠናክሮ እንደሚቀጥል ነው የገለጹት።

በጅቡቲ የኢፌዴሪ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሆነው በቅርቡ የተሾሙት አምባሳደር አብዱልአዚዝ መሃመድ የሹመት ደብዳቤያቸውን ለኢጋድ ዋና ጸሃፊ አምባሳደር ማህቡብ ሟሊም አቅርበዋል።

በዚሁ ወቅት ባደረጉት ውይይትም በቀጠናው እየታየ ስላለው አንጻራዊ ሰላም እና የፖለቲካ መነሳሳት እንዲሁም በኢኮኖሚ ውህደት ረገድ ስለሚደረጉ ጥረቶችም ሃሳብ ተለዋውጠዋል።

በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ ዜጎች ኢጋድ ድጋፍ ማድረግ በሚችልባቸው ጉዳዮች ዙሪያም መመክራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

You might also like
Comments
Loading...