Fana: At a Speed of Life!

አዲሱ የኮንጎ ፕሬዚዳንት በርካታ የፖለቲካ እስረኞችን አስፈቱ

አዲስአበባ፣ መጋቢት 5፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) አዲሱ የኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፖብሊክ ፕሬዚዳንት ፌሊክስ ቲሺሰኬዲ በርካታ የፓለቲካ እስርኞች በነፃ እዲለቀቁ ማድረጋቸው ተገለፀ።

በትናንትናው ዕለት የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃን እንደዘገቡት ከሆነ ሶስት ታዋቂ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮችና ሌሎች 700 የሚሆኑ ተጠርጣሪዎች በነፃ መፈታታቸው ተገልጿል።

ፕሬዚዳንቱ በነፃ እንዲለቀቁ ያደረጓቸው  ሶስቱ ታዋቂ  የተቃዋሚ  ፓርቲ መሪዎችም ፍራንክ ዲኦንጎ፣ዲኦሚንዶንጎላ እና ፊርሚ ያንጋምቢ  የተባሉ መሆናቸው  በዘገባው ተመላክቷል።

የፓርቲ መሪዎቹ ለእስር የተዳረጉትም በቀድሞው ፕሬዚዳንት ጆሴፍ ካቢላ መንግስት ላይ ባካሄዱት ህገ ወጥ ተቃውሞ ምክንያት  መሆኑ ነው የተገለፀው።

በዚህም የካቢላ መንግስት ዲኦንጎ የተባለውም የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ሶስት ወታደሮችን ያለ አግባብ  በማሰር በሚል ክስ  የአምስት ዓመት እስር ፈርዶበት ነበር።

ይሁን እንጂ አዲሱ የካንጎ ፕሬዚዳንት በፊት የነበረውን የፖለቲካ ሁኔታ ለማሻሻል በወሰደው እርምጃ መሰረት  በፖለቲካ ምክንያት የታሰሩ በርካታ ተጠርጣሪዎች በነፃ እንዲፈቱ አድርጓል።

በዚህ መሰረትም ታዋቂ የፖለቲካ አመራሮችን ጨምሮ ከ700 በላይ ተጠርጣሪዎች በነፃ እንዲፈቱ መደረጉ ነው ተገለፀው።

ይህ የፕሬዚዳንት ፌሊክስ ሺሰኬዲ እርምጃም ሀገሪቱን   ወደ ተሻለ  ዲሞክራሲያዊ  አስተዳደር  ሊያመራት ይችላል የሚል ተስፋ ተጥሎበታል።

በሌላ በኩል በካቢላ አስተዳደር ወቅት ፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎችን ሲያከናውኑ የነበሩ  በርካታ የተፎካካሪ ፓርቲ አባሎችና ብሎገሮችና አሁንም በእስር የሚገኙ መሆናቸውን  የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች አስታውቀዋል።

ፕሬዚዳንት ፌሊክስ ቲሺሰኬዲ ባሳለፍነው ታህሳስ ወር በተካሄደው ሀገራዊ ምርጫ የቀድሞ የሀገሪቱን ፕሬዚዳንት ጆሴፍ ካቢላን በማሸነፍ ወደ ስልጣን መምጣታቸው ይታወሳል።

ይህም ኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፖብሊክ ከቅኝ ግዛት ከወጣች በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በዲሞክራሲያዊ ምርጫ ያካሄደቸው ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር ተብሎላታል።

ምንጭ ፦ሬውተርስ

You might also like
Comments
Loading...