Fana: At a Speed of Life!

አይ ኤስ አይ ኤስን ከመጨረሻ ይዞታው ለማስለቀቅ መጠነ ሰፊ ጥቃት እየተሰነዘረበት ይገኛል

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 4፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ)  አይ ኤስ የመጨረሻ ይዞታ በሆነችው ባጉዝ በተባለችው አነስተኛ መንደር ውስጥ ጥቃት እየደረሰበት ነው ተብሏል።

በአሜሪካ የሚደገፈው የሶርያ ዲሞክራሲያዊ ኃይሎች  አይ ኤስን ከባጉዝ ለማስወጣት መጠነ ሰፊ ጥቃት እየሰነዘረ ይገኛል።

ብሪታንያን የሚያህል የቆዳ ስፋት ተቆጣጥሮ የነበረው አይ ኤስ  በ2014 የካሊፌቱን መቀመጫ ራቃ በማድረግ ከምዕራባዊ ሶርያ በመነሳት እስከ ምስራቃዊ ኢራቅ ድረስ ያለውን አካባቢ ተቆጣጥሮ እንደነበር ይታወሳል።

ቀስ በቀስ ይዞታውን ያጣው  አይ ኤስ ሰሞኑን የመጨረሻ ይዞታ በሆነችው ባጉዝ  ከፍተኛ ጥቃት እየደረሰበት ነው።

የጦርነት ቀጠና በሆነችው ባጉዝ በሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች ከመንደሩ እንዲወጡ የተደረገ ቢሆንም አሁንም 2000 የሚደርሱ ሰዎች በዚያ እንዳሉ ተገልጿል።

የሶርያ ዲሞክራሲያዊ ኃይሎች  ኃላፊ በትዊትር መልዕክታቸው እንዳስታወቁት ከሆነ እስከ አሁን 3000 የሚደርሱ የአይ ኤስ ታጣቂዎች እጅ መስጠታቸውንም አስፍረዋል።

በአሜሪካ የሚደገፉት የሶርያ ዲሞክራሲያዊ ኃይሎች በባጉዝ እያደረጉት በሚገኙት ጦርነት  አይ ኤስ የመጨረሻ ሽንፈቱን በመንደሩ ውስጥ እንዲጎነጭ እናደርገዋለን ብለዋል።

 

ምንጭ፦አልጀዚራ

በአብርሃም ፈቀደ

You might also like
Comments
Loading...