Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያና ሱዳን ህገ ወጥ የሰዎችና መሳሪያ ዝውውርን ለመከላከል ወታደሮቻቸውን በጋራ ድንበር ለማስፈር ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 4፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያና ሱዳን የሀገር መከላከያ ኃይሎች በድንበር አካባቢ በጋራ ለመስራት ተስማሙ፡፡

የኢፌዴሪ  መከላከያ ሰራዊት ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል ሰዓረ መኮንን እና የሱዳን አቻቻው ተቀዳሚ ሌትናል ጄኔራል ከማል አብዱል ማውሪፍ አልማሂ በተገኙበት  የኢትዮጵያ እና ሱዳን የሀገር መከላከያ ተቋማት መካከል ለሁለት ቀናት ውይይት አካሂደዋል፡፡

በውይይታቸውም በሁለቱ ሀገራት ድንበር የሚስተዋሉ የሕገ ወጥ ሰዎችና መሳሪያች ዝውውርን ለመግታት እና በድንበር አካባቢ የሚኖር የጸጥታ ችግርን ለማስቆም በጋራ ለመስራት ተስማምተዋል።

ለዚህም በመከላከያ ዘርፍ የጋራ ስራዎችን ለማቀላጠፍ የጋራ ወታደሮቻቸውን በጋራ ድንበር አካባቢዎች ለማስፈር የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡

ከሁለት ሳምንት በኋላ ከሁለቱ ሀገራት የሀገር መከላከያ አባላት የተውጣጡ ባለሙያዎች በገዳሪፍ ሱዳን በመገናኘት የስምምነቱን አፈፃፀም፣ የጋራ ኃይሎቹ የሚሰፍሩባቸውን ቦታዎችና ሌሎች ዝርዝር ጉዳዮች በተመለከተ ውይይት ያደርጋሉ ተብሏል፡፡

ከስብሰባው ጎን ለጎን ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል ሰዓረ መኮንን ከሱዳኑ ፕሬዚዳንት ኦማር ሃሰን አልበሽርን ጋር መወያየታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚነስቴር ያገኘነው  መረጃ ያመላክታል ።

በሁለቱ ተቋማት በኩል የተደረገው ስምምነት በጋራ ድንበር ላይ ሰላምን ከማስፈን ባለፈ ሌሎች ህገ ወጥ ተግባራትን ለመቆጣጠር እንደሚያስችል ፕሬዚዳንት አል በሽር ገልጸዋል።

You might also like
Comments
Loading...