Fana: At a Speed of Life!

አሜሪካ በቦይንግ 737 ማክስ አውሮፓፕላን ላይ ማሻሻያ እንዲያደርግ አዘዘች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት3 ፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአሜሪካ ፌዴራል አቪዮሽን አስተዳደር  በቦይንግ 737 ማክስ አውሮፓፕላን ላይ አስቸኳይ ማሻሻያ እንዲደረግ ትዕዛዝ አስተላለፈ፡፡

ሆኖም አስተዳደሩ በቦይንግ 737 ማክስ የሚደረግ በረራ እንዲቋረጥ የሚለውን ሀሳብ ግን ውድቅ ማድረጉ ነው የተነገረው፡፡

ቦይንግ 737 ማክስ ላይ ኩባንያው ማሻሻያ እንዲያደርግ የተጠየቀው ንብረትነቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሆነ ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን ባሳለፍነው እሁድ መከስከሱን ተከትሎ ነው፡፡

የአሜሪካ ፌዴራል አቪዮሽን አስተዳደር የአደጋውን መንስኤ ለማጣራት ከዓለም አቀፉ የትራንስፖርት ደህነነት ቦርድና ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር እየሰራ ሲሆን÷ ከአውሮፕላኑ አደጋ ጋር የተያያዙ የደህነነት ጉዳዮችን ይፋ እንደሚያደርግ አስታውቋል፡፡

ምርመራውን ተከትሎ ከኩባንያው ጋር የተያያዙ የደህነነት ውጤቶች ከተገኙም ተገቢውን እርምጃና ማስተካከያ እንደሚወሰድም ነው የገለጸው፡፡

የአሜሪካ ፌዴራል አቪዮሽን አስተዳደር   ከዚህ ቀደም ቦይንግ በሶፍትዌሩ ላይ ማሻሻያ እንዲያደርግ ማሳሰቢያ ሰጥቶት እንደነበረ ነው ያስታወቀው፡፡

ከአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተነስቶ ወደ ኬኒያ በማምራት ላይ እንዳለ ደብረዘይት አካበባቢ በተከሰከሰው ቦይንግ 737 አውሮፕላን አደጋ የ157 ሰዎች ሕይወት አልፏል፡፡

በዚህም በዓለም አቀፍ ደረጃ የቦይንግ 737 ማክስ ተጠቃሚዎች ላልተወሰነ ጊዜ አገግሎት እንዳይሰጥ በማድረግ ላይ መሆናቸውም ተነግሯል፡፡

ምንጭ፡ አልጀዚራ

You might also like
Comments
Loading...