Fana: At a Speed of Life!

ማክሮሶፍት የስልካችንን የአንድሮይድ መተግበሪያ በዊንዶውስ 10 ኮምፒውተር ላይ መጠቀም የሚያስችል ማሻሻያ ይፋ አደረገ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 4፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ማክሮሶፍት የስማርት ስልካችንን የአንድሮይድ መተግበሪያዎች በዊንዶውስ 10 ኮምፒውተር ላይ መጠቀም የሚያስችል ማሻሻያ ይፋ አደረገ።

በአዲሱ የማይሮሶፍት ዊንዶውስ 10 አገልግሎትም የስልካችንን ስክሪን ኮምፒውተራችን ላይ በማምጣት መጠቀም የሚያስች ነው ተብሏል።

አዲሱ የማርክሮሶፍት ዊንዶውስ 10 ከኮምፒውተር ጋር የማገናኘት አገልግሎትን የሳምሰንግ ጋላክሲ S8፣ S8 ፕላስ፣ S9፣ እና S9 ፕላስ ስልኮችን ያላቸው ሰዎች ብቻ ናቸው ለጊዜው መጠቀምጅ የሚችሉት።

ይህንን አገልግሎት ለመጠቀምም ኮምፒውተራችን እና ስማርት ስልካችን የግድ መገናኘት አለባቸው።

ምንጭ፦ fossbytes.com

You might also like
Comments
Loading...