Fana: At a Speed of Life!

ለልማት ስራዎች ከይዞታቸው ለተነሱ ዜጎች ካሳና ምትክ ቦታ ለመስጠት መዘጋጀቱን የአዳማ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 6፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ለልማት ስራዎች ከይዞታቸው ለተነሱ ዜጎች ካሳና ምትክ ቦታ ለመስጠት መዘጋጀቱን የአዳማ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ።

የአዳማ ከተማ ከንቲባ አቶ መስፍን አሰፋ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር በነበራቸው ቆይታ ካሳ ላልተከፈላቸው 144 ዜጎች የከተማ አስተዳደሩ ምትክ ቦታም እንዲሰጣቸው ውሳኔ አስተላልፏል ብለዋል።

በቀጣይም በከተማዋ በልማት የሚነሱ ዜጎች እንደሚኖሩ በመግለጽ ለተነሺዎች ተገቢው ምትክና ካሳ ክፍያ እንደሚፈጸም ተናግረዋል።

የከተማ አስተዳደሩ አስፈላጊው ምትክና ካሳ ክፍያ እንዲፈጸም ውሳኔ ያስተላለፈው ለኢምንዱስትሪ ፓረክ ልማት ተነሽዎች መሆኑንም ከንቲባው ገልጸዋል።

ለልማት ተነሺዎች የሚሰጡ ምትክ ቦታዎችም ቀደም ብለው የመብራት፣ የውሃና ሌሎች መሰረተ ልመቶች እንደሚሟሉላቸው ነው አቶ መስፍን የሚናገሩት።

መንግስት የመሰረተ ልማት ግንባታዎችን ለማከናወን ሲፈልግ ለግለሰቦች የመኖሪያና የመስሪያ ቦታና ተቋማት እስካሁን ባለው አሰራርም የካሳ ክፍያ ሲፈጸም መቆየቱ ይታወቃል።

ይሁን እንጂ የካሳ አከፋፈል ሰርዓቱ ወጥነት የሌለው ከቦታቸው ለሚነሱ ዜጎች የሚሰጠው ካሳም ግለሰቦችና ተቋማት ያጡትን ነገር የማያካክስ እንዲሁም ከቦታ ቦታ ያለውን የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታን ከግምት ውስጥ ያላስገባ ነው የሚሉ ትችቶች ሲቀርቡበት እንደነበረ ይታወሳል።

ማንኛወም ዜጋ ለልማት ከሚኖርበት ከአካባቢው ሲነሳ ቀድሞ ከነበረው ህይወት በተሻለ ደረጃ መኖር አለበት የሚል አቋም መያዙን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዳይሬክተር ወይዘሪት ሌሊሴ ነሜ ይናገራሉ።

ለልማት የሚነሱ ዜጎች ካሳና ምትክ ቦታ በከተማ አስተዳደሮች ተክፍሏቸው በሚከፈተው ልማት የመጀመሪያው የስራ አድል ተጠቃሚ መሆን እንዳለባቸውም ተናግረዋል።

ዜጎች ከይዞታቸው ተነስተው ካሳም ሆነ ምትክ ቦታ ማገኘታቸው በማንኛውም የልማት ስራ የኔነት እንዲሰማቸውና በልማቱ ተሳታፊ እንዲሆኑ ያሰችላል ሲሉም ዳይሬክተሯ ገልጸዋል።

 

በታሪክ አዱኛ

You might also like
Comments
Loading...