Fana: At a Speed of Life!

የአስተዳደር ወሰንና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን ከኢንጂነር ታከለ ኡማ ጋር ተወያየ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 8 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የአስተዳደር ወሰንና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ጋር ተወያየ።

ኮሚሽኑ ከተቋቋመ ወዲህ እየሰራቸው ያሉ ስራዎችን በተመለከተ እና የከተማ አስተዳደሩ የሚጠበቅበትን ማድረግ በሚገባው ጉዳዮች ላይ ነው መክሯል።

የአሁኑ ውይይት እንደ ትውውቅ የሚታይ ሆኖ ወደ ፊት አብሮ መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ነው የመከረው።

የኮሚሽኑ ሰብሳቢ ዶክተር ጣሰው ገብሬ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት፥ የከተማ አስተዳደሩ ከኮሚሽኑ ጋር በጋራ ለመስራት ያለውን ዝግጁነት አሳይቷል።

ይህም ለኮሚሽኑ ቀጣይ ስራ አጋዥ እንደሚሆን ተናግረዋል።

ኮሚሽኑ የአስተዳደር ወሰን እና የማንነት ጉዳዮችን በተመለከተ የውሳኔ፣ የምክረ ሃሳብ እና የመፍትሄ ሃሳቦችን ለሚመለከታቸው አካላት የማቅረብ ስራ እንደሚሰራ ገልጿል።

ከዚህ ባለፈም የሚቀርቡለትን ጉዳዮች ለመፍታት ከሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ጋር ከሚያደርገው ምክክር በተጨማሪ ከህብረተሰቡ ጋር ውይይቶችን በማካሄድ ግብዓቶችን እንደሚሰበስብም ነው የገለጸው።

በሀብታሙ ተክለስላሴ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.