Fana: At a Speed of Life!

የሰላም ሚኒስቴር ለሙዳይ በጎአድራጎት ማህበር የተለያዩ ቁሳቁሶችን ድጋፍ አደረገ  

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 1 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰላም ሚኒስቴር ለሙዳይ በጎአድራጎት ማህበር የተለያዩ ቁሳቁሶችን ድጋፍ አድርጓል ፡፡

ሙዳይ በጎ አድራጎት ማህበር ጎዳና ላይ ወድቀው በልመና የተሰማሩና በሴተኛ አዳሪነት ህይወታቸውን ሲገፉ የነበሩ እናቶችን ከነልጆቻቸው ከችግር ውስጥ በማውጣት አዲስ ህይወት እንዲጀምሩ  በማድረግ  ላይ ይገኛል፡፡

የሰላም ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮችም  በሙዳይ በጎ አድራጎት ማህበር በመገኘት ለመተኛ የሚሆኑ ቁሳቁሶችና አልባሳትን ድጋፍ አድርገዋል።

ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል ከራስ በላይ ለሌሎች መኖርን በተግባር ላሳየን ለሙዳይ በጎአድራጎት ማህበር እውነተኛ እራስን የመስጠት ፍቅር ስላደረጉ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ህጻናቶችንና እናቶችን መደገፍ ለቤተሰብ መቃናት ትልቅ ትርጉም ያለው በመሆኑ አቅም በፈቀደ መጠን ድጋፉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡

አያይዘውም ከዚህ ማህበር የምንማረው ለመረዳዳትና ለመደጋገፍ ዋናው ነገር ፍቅር በመሆኑ ሁላችንም ባለን አቅም እነዚህን የመሰሉ መልካም አርዓያ የሆኑትን በእውቀት፣ በገንዘብና በጉልበት  እንደግፍ  ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የማህበሩ መስራች ወይዘሮ ሙዳይ ምትኩ ሚነስትር መስሪያቤቱ ላደረገላቸው ድጋፍ ምስጋና ማቅረባቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.