Fana: At a Speed of Life!

በ200 ሚሊየን ብር ወጪበአፋር ክልል የድንበር ተሻጋሪ ተሽከርካሪዎች ተርሚናል ግንባታ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 4 ፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ)የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል የሚረዳ የድንበር ተሻጋሪ የጭነት ተሸከርካሪዎች ተርሚናል ግንባታ በአፋር ክልል ኤሊደአር ወረዳ ዲችኦቶ ከተማ ተጀምሯል።

ግንባታውን ያስጀመሩት የትራንስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ÷ የተርሚናሉ ግንባታ ድንበር ተሻጋሪ አሸከርካሪዎችና ቤተሰቦቻቸው እንዲሁም ህብረተሰቡን የበሽታው ተጋላጭነት ለመቀነስ የላቀ ሚና እንደሚኖረው ነው የጠቆሙት።

በቀን ከአንድ ሺህ በላይ ድንበር ተሻጋሪ ተሸከርካሪዎችን የማስተናገድ አቅም የሚኖረውና ግንባታው በአንድ ወር ውስጥ ተጠናቆ ለአገልግሎት እንደሚበቃ ይጠበቃል።

የተሽከርካሪዎች ማቆያና በሂደትም ለሾፌሮች የመታጠቢያ፣ ማረፊያ፣ ምግብ፣ ጤና ምርመራና ህክምና አገልግሎቶችን የሚሰጥ ነው ነው ብለዋል።

በምስራቅ አፍሪካ ደረጃውን የጠበቀ   ተርሚናል ለማድረግ የሚስፋፋ መሆኑን ሚኒስትሯ አስታውቀዋል።

የአካባቢው ህብረተሰብና የአስተዳደር አካላት እንደጅምሩ ሁሉ ለግንባታው በስኬት መጠናቀቅ አስፈላጊውን ትብብር እንደሚያደርጉ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።

የትራንስፖርት ሚኒስትር ደኤታ አቶ አወል ወግሪስ በበኩላቸው÷ ክልሉ በጋላፊ በኩል የሀገሪቱ ከ90 በመቶ በላይ ወጪና ገቢ የንግድ እንቅስቃሴ የሚካሄድበትና በቀን እስከ 2ሺህ ተሽከርካሪዎች የሚተላላፉበት ትራንስፖርት ኮሪደር መሆኑን ገልጸዋል።

በጅቡቲ ካለው የኮሮና ቫይረስ ስርጭት መስፋፋትጋር ተያይዞ አሸከርካሪዎች የሚኖራቸው ቆይታ በተራዘመ ቁጥር ለአላስፈላጊ ወጪ ከመጋለጥ በላይ ለተያያዥ የጤና እክል እያደረጋቸው በመሆኑ የተርሚናሉ ግንባታ ይህን ችግር ለመፍታት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ተናግረዋል።

ተርሚናሉ 200 ሚሊዮን ብር ያህል ወጪ የሚደረግበት ሲሆን በ16 ሄክታር መሬት ላይ የሚያርፍ መሆኑን ከትራንስፖርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.