Fana: At a Speed of Life!

ፖላንድ ከአሜሪካ በ414 ሚሊየን ዶላር የተለያዩ የጦር መሳሪያዎችን ግዥ ልትፈፅም ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 4፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ፖላንድ በ414 ሚሊየን ዶላር ከአሜሪካ የተለያዩ የጦር መሳሪያዎችን ግዥ ልትፈፅም መሆኑ ተገለፀ።

ፖላንድ ከአሜሪካ የተለያዩ መጠን ያላቸው ዘመናዊ የጦር መሳሪያዎችን ለመግዛት ዝግጅት ላይ መሆኗንM የሀገሪቱ የመከላከያ ሚኒስትሩ ማሪውዝ ብላዛክ ተናግረዋል።

የጦር መሳሪያ ግዥውም የሀገሪቱን የመከላከያ ሰራዊት ሁለንተናዊ አቅም ለማሳደግ ያለመ መሆኑ ነው የተገለፀው።

ሀገሪቱ ለመግዛት ያቀደቻቸው የጦር መሳሪያዎችም የተለያዩ ዘመናዊ ረጅም ርቀት ተወንጫፊ ሮኬቶችን ጨምሮ በርካታ ላውንቸሮችንና ሌሎች ማሳሪያዎችን የሚያካትት መሆኑን ተገልጿል ።

ሁለቱ ሀገራት ከሩሲያጋር የገቡበትን ውዝግብ ተከትሎ በቀጠናው ያለውን ችግሩ ለማስወገድ ወታደራዊ አቅምን ማጎልበት አስፈላጊ መሆኑንም በአንክሮ ተናግረዋል ።

ከዚህ ባለፈም በቀጠናው ያለውን የፀጥታና ደህንነት ችግር ለመፍታት ከአሜሪካና ከሌሎች ሀገራት ጋር በቅንጅት ለመስራት ፈቃደኛ መሆናቸውን ጠቁመዋል ።

ፖላንድ ባለፈው የፈረንጆች ዓመት በ4 ነጥብ 75 ቢሊየን ዶላር አሜሪካ ሰራሽ ፀረ ሚሳኤል የጦር መሳሪያዎችን ለመግዛት መፈራራሟ ይታወሳል ።

ምንጭ ፦presstv.com

You might also like
Comments
Loading...