Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ የኮሪያ ወርልድ ቪዥን የልዑካን ቡድን ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 21፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የኮሪያ ወርልድ ቪዥን የልዑካን ቡድን አባላት ጋር ተወያዩ።

ኮሪያ የሚገኘው የወርልድ ቪዥን ቢሮ በተለያዩ የኮሪያ በጎ አድራጎት ድርጅቶችና ግለሰቦች በየዓመቱ በሚደረግ ዝግጅት የተገኘን ገቢ በመላክ በኢትዮጵያ በሚገኘው ወርልድ ቪዥን ለሚያከናውናቸው የልማት ስራዎች እገዛ ሲያደርግ ቆይቷል።

በዚህ እንቅስቃሴ ውስጥ ጉልህ ድርሻ ያላቸው ከዶንግ ያንግ ዕለታዊ ጋዜጣ እና የዶንግ ያንግ ከተማ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች የተካተቱበት ቡድን በኢትዮጵያ የሚከናወኑ የልማት ስራዎችን ለማየት ነው ወደዚህ የመጣው።

ቡድኑ እስከ አሁን ላደረጋቸው ድጋፎችም ክብርት ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

በቀጣይነትም ከዚህ በሰፋ መልኩ በኢትዮጵያ ለሚካሄዱ የልማት ስራዎች ሚናውን እንደሚያሳድግ ያላቸውን እምነት መግለጻቸውን ከፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

You might also like
Comments
Loading...