Fana: At a Speed of Life!

ፌስ ቡክ የመጀመሪያውን የይዘት መገምገሚያ ማዕከል በኬንያ ሊከፍት ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 1፣ 2011 (ኤፍ ቢ ሲ) ፌስ ቡክ የመጀመሪያውን የይዘት መገምገሚያ ማዕከል በኬንያ ሊከፍት ነው።

ፌስ ቡክ ከሰሃራ በታች በሚገኙ የአፍሪካ ሀገራት ውስጥ የመጀመሪያ የሆነውን የይዘት መገምገሚያ ማዕከል በኬንያ ሊከፍት መሆኑን አስታውቋል።

ማዕከሉ በቀጠናው የሚገኙ የፌስ ቡክ ተጠቃሚዎች በመተግበሪያው የሚያስተላልፉትን ይዘት ለመገምገም የሚያስችል ነው ተብሏል።

ይህም ፌስ ቡክ በአካባቢው የሚገኙ ደንበኞቹ በመተግበሪያው አማካኝነት ሀሳባቸውንና መልዕክታቸውን ያለምንም ችግር በነጻነት እንዲያስተላልፉ የሚያስችል መሆኑ ነው የተገለፀው።

ማዕከሉ በያዝነው የፈረንጆች ዓመት መጨረሻ አካባቢ 100 የሚሆኑ ባለሙያዎችን የሚቀጥር መሆኑም ተነግሯል።

በዚህ ማዕከልም ሶማሊኛ፣ ኦሮምኛ፣ ዋውሳ እና ስዋህሊልኛን ጨምሮ በበርካታ ቋንቋዎች አገልግሎት የሚሰጥ መሆኑ ነው የተገለፀው።

ምንጭ ፦shega.org

You might also like
Comments
Loading...