Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ ከተመድ ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉቶሬዝና ከተለያዩ ሀገራት መሪዎች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 3፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከአፍሪካ ህብረት ጎን ለጎን ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ጋር ተወያዩ፡፡

ከውይይቱ በኋላ ዋና ፀሀፊው እንደተናገሩት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ኢትዮጵያ በቀጠናው ሰላምና ፀጥታን ለማረጋገጥ የምታደርገውን ጥረት ይደግፋል ብለዋል፡፡

በተመሳሳይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከፍሊስጤሙ ፕሬዚዳንት ሙሀሙድ አባስ እና ከተባበሩት አረብ ኤምሬትስ የዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር ሪም አልሀሺሚ ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አካሂደዋል፡፡

ከስብሰባው ጎን ለጎን ከተለያዩ አካላት ጋር ውይይት እያደረጉ የሚገኙት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከደቡብ አፍሪካው ፕሬዚዳንት ሲሪያ ራማፎሳ ጋር ተወያያተዋል፡፡

እንዲሁም ከኬንያው ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ጋር በሁለትዮሽ፣ አካባቢያዊ እና አለም አቀፍ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አድርገዋል፡፡

 

በሶዶ ለማ በምስክር ስናፍቅ

You might also like
Comments
Loading...