Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዶክተር አብይ ከተለያዩ ሃገራት ፕሬዚዳንቶች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 4 ፣ 2011 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከተለያዩ ሃገራት ፕሬዚዳንቶች ጋር ተወያይተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ እየተካሄደ ካለው 32ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ጎን ለጎን፥ ከቦትስዋናው ፕሬዚዳንት ሞግዌትሲ ማሲሲ፣ ከሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሞሃመድ አብዱላሂ ፋርማጆ፣ ከጂቡቲው ፕሬዚዳንት እስማኤል ኦማር ጊሌ፣ ከቱኒዚያው ፕሬዚዳንት ቤጂ ካይድ ኢሴብሲ እንዲሁም ከጋናው ፕሬዚዳንት ናና አኩፎ አዶ ጋር ተወያይተዋል።

ከሱዳኑ ፕሬዚዳንት ኦማር ሃሰን አልበሽር ጋርም በሁለትዮሽና የጋራ ጉዳዮች ላይ መክረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አሕመድ ከቦትስዋና፣ ከአልጄሪያ ፣ ከሞሮኮ ፣ ከቱኒሲያና ከኤስቶንያ መሪዎች ጋር በጋራ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸው ወቅትም በሁለትዮሽና አህጉራዊ ጉዳዮች ላይ መክረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከህብረቱ ጉባኤ ጎን ለጎን ከተለያዩ ሃገራት መሪዎች ጋር በትናንትናው እለትም ተወያይተዋል።

በዚህ መሰረት ከፍልስጤም ፕሬዚዳንት ማህሙድ አባስ: ከደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳና ከኬንያው ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ጋር የሁለትዮሽ ውይይቶችን አካሂደዋል።

ከዚህ ባለፈም ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬስ ጋር ተገናኝተው ስለ ተመድ ቀጣይ ድጋፍ ተወያይተዋል።

Photo credit; Office of the Prime Minister-Ethiopia

You might also like
Comments
Loading...