Fana: At a Speed of Life!

ዶ/ር ወርቅነህ ከአሜሪካ ብሄራዊ ደህንነት ምክር ቤት የፕሬዚዳንቱ ረዳትና የአፍሪካ ጉዳዮች ከፍተኛ የደህንነት ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣የካቲት 5፣2011 (ኤፍ ቢ ሲ) ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ከአሜሪካ ብሄራዊ ደህንነት ምክር ቤት የፕሬዚዳንቱ ረዳት እና የአፍሪካ ጉዳዮች ከፍተኛ የደህንነት ዳይሬክተር ሲይሪሊ ሳርቶር ጋር ተወያዩ።

በውይይታቸውም በሁለትዮሽ እና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ዙሪያ መምከራቸው ነው የተገለፀው።

በኢትዮጵያ እና አሜሪካ መካከል ያለው ታሪካዊ እና ስትራቴጅካዊ ግንኙነት በኢኮኖሚ ዘርፍም ይበልጥ ለማጠናከር መስራት  እንደሚገባ ዶክተር ወርቅነህ  ተናግረዋል ።

አሜሪካ ለኢትዮጵያ በተለያዩ  ዘርፎች ላይ እያደረገች ላለው ድጋፍም ምስጋና ማቅረባቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል ።

ሲይሪሊ ሳርቶር በበኩላቸው በአሁኑ ስዓት በኢትዮጵያ  እየተካሄደ ያለውን ሁለንተናዊ ለውጥ አድንቀዋል።

ከዚህ ባለፈም አሜሪካ ከኢትዮጵያ ጋር የምታደርገውን ትብብር በሁሉም ዘርፍ ይበልጥ አጠናክራ የምትቀጥል መሆኑን ጠቁመዋል።

You might also like
Comments
Loading...