Fana: At a Speed of Life!

የ4ኛው ህዝብና ቤት ቆጠራ ተሳታፊዎች ስልጠና በባህር ዳር ከተማ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 7፣2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአራተኛው ህዝብና ቤት ቆጠራ ተሳታፊዎች ስልጠና በባህር ዳር ከተማ ተጀመረ ፡፡

በአማራ ክልል አመራር ኢንስቲትዩት ማዕከል የምዕራብ አማራና የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአራተኛው ህዝብና ቤት ቆጠራ ተሳታፊዎች ስልጠና ዛሬ ተጀምሯል፡፡

በዚህ የሥልጠና መርሃ ግብር የመክፈቻ ፕሮግራም ላይ የተገኙት የአማራ ክልል መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አሰማኸኝ አስረስ ሰልጣኞቹ በቆጠራው ችግሮች እንዳይከሰቱና የታሪክ ተወቃሽ እንዳይሆኑ ከወዲሁ ቅድመ ጥንቃቄና ዝግጅት ማድረግ እንደሚገባቸው ተናግረዋል፡፡

ለዚህም ለህብረተሰቡ በሚገባው መንገድ የትምህርትና ቅስቀሳ ስራዎች መስራት እንዳለባቸው ነው የገለጹት፡፡

ትክክለኛውን መረጃ ለትክክለኛው አካል ለማድረስ ሁሉም የየበኩሉን ሚና መወጣት እንዳለበትም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

በሦስተኛው ዙር የህዝብና ቤት ቆጠራ የታዩ ክፍተቶችን ዳግም መከሰት እንደሌለባቸው የተናገሩት አቶ አሰማኸኝ ይህንን ቆጠራ የቆጠርንም ያስቆጠርንም እኛው ነን ብለዋል፡፡

ሦስተኛው የህዝብና ቤት ቆጠራ በርካታ ችግሮች የነበሩበት፣ ብዙ ያነጋገረ እንደነበረም አስታውሰዋል፡፡

ስለሆነም ከዚህ ችግር በመማር በአራተኛው ዙር የህዝብና ቤት ቆጠራ ተመሳሳይ ችገሮች እንዳይከሰቱ ሰልጣኞቹ ከወዲሁ ቅድመ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባቸው ነው የተነገሩት፡፡

በናትናኤል ጥጋቡ

You might also like
Comments
Loading...