Fana: At a Speed of Life!

የፀረ-ሽብር አዋጅን ለማሻሻል በወጣው ረቂቅ ላይ ውይይት እየተደረገ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 21፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የፀረ-ሽብር አዋጅን ለማሻሻል በወጣው ረቂቅ አዋጅ ላይ ውይይት እየተደረገ ነው።

 
ረቂቅ አዋጁ ከድርጅቶች አሰያየም እስከ ተጠርጣሪዎች አያያዝ ከቀድመው ሕግ የተለዩ ድንጋጌዎችን የያዘ መሆኑ ነው የተገለጸው።
 
የሽብር ተግባርን ማቀድና መደገፍ ላይ ተጠርጣዎችን እንደየተሳትፏቸው ተጠያቂ የሚያደረጉ ድንጋጌዎች የተካተቱበት መሆኑንም ከውይይቱ መረዳት ተችሏል።
 
የሽብር ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ከዚህ ቀደም ወጥቶ ከነበረው “የፀረ-ሽብርተኝነት አዋጅ ቁጥር 652/2001″ በርከት ያሉ ማሻሻያዎች የተደረጉበት እንደሆነም ተገልጿል።
 
ምሁራን፣ የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች እየተወያዩበት ያለው አዲሱ ረቂቅ አዋጅ አዳዲስ አንቀጾች የተካተቱበት ሲሆን፥ በ2001ዓ.ም በወጣው አዋጅ አሻሚ የነበሩ ጉዳዮች ላይ ግልጽና ሰፊ ማብራሪያ የሚሰጥ እንደሆነ ከውይይት መርሃ ግብሩ መረዳት ተችሏል።
 
በ”ፀረ-ሽብርተኝነት አዋጅ ቁጥር 652/2001” ላይ ከተለያዩ አካላት ቅሬታ ሲቀርብበት የነበረ መሆኑ በውይይቱ ተነስቷል።
 
በዚህም የተለያዩ ጥናቶች ሲደረጉ ከቆዩ በኋላ አዲሱ ረቂቅ አዋጅ መዘጋጀቱ አስፈላጊ ሆኖ መገኘቱ ነው የተገለጸው።
 
በአዲሱ የፀረ ሽብር ረቂቅ መሰረት ማንኛውም ሰው የፖለቲካ፣ የሃይማኖትና ሌሎች ዓላማዎች ለማራመድ ህዝብን ወይንም የተሰወነ አካላትን ማሸበር፣ መንግስትን በማስገደድ፣ አካል ጉዳት ያደረሰ፣ የሰውን ህይወት ለአደጋ ያጋለጠ፣ ያገተ፣ የጠለፈ፣ የሽብር ድርጊት እንደፈጸመ እንደሚቆጠር ረቂቁ አካቷል።
 
በንብረት፣ በተፈጥሮ ሀብትና አካባቢ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደረሰ እንዲሁም፥ የህዝብ አገልግሎት እንዲስተጓጎል ያደረገ ማንኛውንም አካል ከ10 እስከ 18 ዓመት ጽኑ እስራት እንደሚቀጣ የሚደነግግ ነው።
 
ከዚህም ሌላ ባህላዊ ቅርፆችና መሰረተ ልማት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደረሰ አካል ተጠያቂ እንደሚያደርግ በረቂቁ ተቀምጧል።
 
የሽብር ድርጊት ለመፈፀም መዛት፣ ማቀድ፣ መዘጋጀት፣ ድጋፍ ማድረግ፣ ማነሳሳትና የመሳሳሉት ድርጊቶች ተጠያቂ ሚያደረጉ ሆነው አሻሚነት በሌለው መንገድ መቀመጣቸው ተገልጿል።
 
ልዩ የምርመራ ዘዴዎችን የተመለከቱ ማብራሪያዎችን የያዘው ረቂቅ አዋጁ በጠቋሚ፣ ምስክር፣ በዳኝነትና ህግ አስፈፃሚ አካላት ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎችን መከላከል የሚያስችሉ አንቀፆች የተካተቱበት ነው።
 
ተጠርጣሪዎች በምን አግባብ መያዝ አለባቸው፣ በብሄራዊ ጸረ ሽብር ኮሚቴና የአስፈፃሚ አካለት አስራር ላይ ሰፊ ማብራሪያ የሚሰጠው አዲሱ ረቀቅ አዋጅ ተጠርጣሪዎቹ በብሄራዊ መረጃ ደህንነት እንዲያዙ ያደርግ ያነበረውን አሰራር የሚያስቀር መሆኑም ታውቋል።
 
 
በአወል አበራ
You might also like
Comments
Loading...