Fana: At a Speed of Life!

የጤና ሚኒስትር ዶክተር አሚር አማን ከቢል ጌትስ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 3፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የጤና ሚኒስትር ዶክተር አሚር አማን ከቢል ጌትስ ጋር ተወያዩ።
 
የጤና ሚኒስትሩ ከቢል እና ሜሊንዳ ፋውንዴሽን መስራች ቢልጌትስ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ መነጋገራቸውን አስታውቀዋል።
 
በውይይታቸውም በኢትዮጵያ የመሰረታዊ ጤና አገልግሎት ዙሪያ አትኩረው ተወያይተዋል።
 
በዚህም በሀገሪቱ የመሰረታዊ ጤና አገልግሎት ተደራሽነትን በጥራት እና በአገልግሎት ስፋት በማሳደግ ዙሪያ ውይይት አድርገዋል።
 
የጤና ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ ከጤናው ዘርፍ ጋር ላሳልፉት የ15 ዓመታት የተጠናከረ ግንኙነት ቢልጌትስን አመስግነዋል።
 
ቢል ጌትስ በትናትናው ዕለት ከኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ እና ከኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።
 
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባሳለፍነው ጥር ወር በስዊዘርላንድ ዳቮስ በነበራቸው ቆይታም የቢልና ሚሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን ተባባሪ ሊቀመንበር ከሆኑት ቢል ጌትስ ጋር ተገናኝተው መወያየታቸው ይታወሳል።
 
በውይይታቸውም በግብርና፣ መስኖና ቴክኖሎጂ ዘርፎች ለመተባበር መስማማታቸው የሚታወስ ሲሆን፥ ትናንት ያደረጉት ውይይትም በዳቮስ የጀመሩትን ውይይት የቀጠለ ስለመሆኑ ተነግሯል።
 
በመጨረሻም ጠቅላይ ሚኒስትሩ የቢልና ሚሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን በኢትዮጵያ በጤና፣ ግብርና እና አቅም ግንባታ ዘርፎች ለሚያደርገው ድጋፍ አመስግነዋል።
 
በአብርሃም ፈቀደ
You might also like
Comments
Loading...